Bible

 

ማቴ 2

Studie

   

1-2 ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል። የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተ እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

3 ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤

4 የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።

5-6 እነርሱም። አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።

7 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥

8 ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ። ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።

9 እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።

10 ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።

11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

12 ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።

13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።

14-15 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ። ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

16 ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።

17-18 ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ

19 ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ።

20 የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።

21 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።

22 በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤

23 በነቢያት። ዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

   

Ze Swedenborgových děl

 

Scriptural Confirmations # 12

  
/ 101  
  

12. 10. Thou shalt call His name Jesus, He shall save the people from their sins (Matthew 1:21).

The wise men came to adore the infant Jesus, and that He would be born in Bethlehem according to Micah 5:1 (Matthew 2:1-6).

The wise men adored Him and brought Him gifts (Matthew 2:11).

Jesus said to John, It becometh us so to fulfil all the justice of God (Matthew 3:15).

Jesus said to the devil who was tempting, Thou shalt not tempt the Lord thy God; and again, Thou shalt adore the Lord thy God, and Him only shalt thou serve (Matthew 4:7, 10).

A ruler came and adored Jesus (Matthew 9:18).

He that receiveth Me receiveth Him that sent Me (Matthew 10:40).

All things are delivered unto Me by my Father, wherefore come ye all unto Me (Matthew 11:27-28).

They that were in the ship adored Jesus, saying, Of a truth Thou art the Son of God (Matthew 14:33). A woman of Canaan (Matthew 15:25), the disciples (Luke 24:52), a blind man (John 9:38), adored Him.

Multitudes glorified the God of Israel (Matthew 15:31). There is one Rabbi and one Master, that is, He teaches what is good and true (Matthew 23:8,10).

Of the sign of the coming of the Lord and of the consummation of the age (Matthew 24:1 to end).

Then shall there be wars and rumor, and they will say, I am the Christ; false prophets shall arise and seduce many; signifies the heresies in the first times, which were many (Matthew 24:5-14).

The women, running to Jesus, adored Him (Matthew 28:9).

He said, All power is given unto Me in heaven and on earth (Matthew 28:18; Psalms 8:6-7).

  
/ 101  
  

Thanks to the Swedenborg Foundation for their permission to use this translation.